የኢትዮጵያ ነፃነትና አንድነት ሃይል በወያኔ ይዞታ ላይ ባካሄደው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ፣
የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ሃይል በመተማ ከተማ በወያኔ ይዞታ ላይ በሰነዘረው ከፍተኛና ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ፣ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገቡን ተገለፀ። በግንባሩ ዘመቻ አስተባባሪ ገለፃ መሠረት፣ ረቡዕ ሚዝያ 3 ቀን 2004 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰአት፣ በመተማ ከተማ የአንድነት ሃይሉ ባካሄደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ፣ ወያኔ በደረቅ ወደብነት የሚገለገልበትን ከፍተኛ የንብረት ዲፖና ሌሎች 25 ተመሳሳይ መደብርሮች ሙሉ በሙሉ ከጠጥቅም ውጭ ሆነዋል። በተጨማሪም፣ በዚሁ ጥቃት መሠረት በተለምዶ ካርቱም ሆቴል እየተባለ የሚታወቀውና ንብረትነቱ ወ/ሮ ጸሐይ የምትባል የወያኔ ደህንነት አባልና ዋና የመረጃ ምንጭ የሆነች አብሮ ተቃጥሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከፊት ለፊቱ የሚገኘው አቶ ሃዲሽ ብርሃኔ የተባለው ነባር የወያኔ ታጋይና በ1993 ዓ.ም የአካባቢው አስተዳዳሪ የነበረ፣ ቀንደኛ የወያኔ ጋሻ ጃግሬና የደህንነት አባል፣ ትልቅ መደብር ጭምር አብሮ የጋዬ መሆኑን አስታውቀዋል። ግንባሩ በወሰደው በዚህ ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡንና በግጭቱም ከፍተኛ የሰውና የንብረት ጉዳት በወያኔ ሃይልና ደጋፊዎቹ ላይ አድርሶ በሰላም ወደካምፑ መመለሱን አስታውቀዋል።
ግንባሩ ቀደምም ሲል በሚያዝያ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በተመሳሳይ በሱዳን ጠረፍ አካባቢ ተንቀሳቅሶ የነበረና ሲሆን፣ ወያኔ በማናለብኝነት ለባእዳን በመሸጥ ላይ የሚገኘውን ለም የሀገሪቱን መሬት እና የጥፋት ተልእኮ ለማክሽፍ በወሰደው የሀይል እርምጃ፣ የገዳሪፍ (ሱዳን) አስተዳዳሪ ለሱዳን የሰጠውን መሬት ለመረከብ በአምራኩባ በኩል ወደኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው ሲገቡ ሲሉ ልዩ ሥሙ ባሶንዳ እየተባለ በሚጠራው ሥፍራ ደፈጣ በማድረግ በሰነዘረው ማጥቃት፣ 6 የሱዳን ወታደሮች ቆስለው እንደነበርና፣ ከስድስቱ መሃል አንዱ ሲሞት ሌሎች 5 በገዳሪፍ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።
No comments:
Post a Comment