የ12 ሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ 14 ሰው ቆሏል፣ 52 ቤት ተቃጥሏል እንዲሁም ከ1500 ሰዎች በላይ ተፈናቅለዋል ተብሏል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በአምስት ወረዳዎች ሰሞኑን ይደረጉ የነበሩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መልካቸውን ቀይረው የአካባቢው ተወላጆች በሆኑና ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈፀሙ ከተለያየ ቦታ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። ከጥቅምት 10 እስከ 11 ባሉት ቀናት ከፍተኛ ረብሻ እንደነበርም ታውቋል።
የዞን አስተዳደር እንዳስታወቀው በግጭቱ 12 ሰው ሞቷል። 14 ሰው ቆስሏል። 52 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከ1500 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።
የሞቱትና የቆሰሉት ሰዎች የተለያየ ብሔር ያላቸው ናቸው ተብሏል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይሰራጩ የነበሩት ምስሎች ከሌላ ሀገር የተወሰዱ ናቸው ሲሉ የክልል ባለስልጣናት ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
No comments:
Post a Comment